ሩዋንዳ ከቻይና ኩባንያዎች ጋር በመተባበር በኤሌክትሪክ የሚሰሩ የአየር ላይ ታክሲ የሙከራ አገልግሎትን አስጀምራለች።
የአየር ላይ ታክሲው ፓይለት ሳይኖረው በምድር ላይ በሚኖር መቆጣጠሪያ አገልግሎት እንደሚሰጥም ተመላክቷል።
በሩዋንዳ ኪጋሊ ከተካሄደው የአቪዬሽን አፍሪካ 2025 የመሪዎች ጉባዔ ጉን ለጎን ቴክኖሎጂው ላይ ሙከራ ተደርጓል።
በጉባዔው ላይ ንግግር ያደረጉት የሩዋንዳው ፕሬዚዳንት ፖል ካጋሜ “ቴክኖሎጂው የአፍሪካን የወደፊት የአቪዬሽን አቅም ያጎለብታል” ብለዋል።
የአየር ላይ ትራንስፖርት ገበያው የአፍሪካ አህጉራዊ ነፃ የንግድ ቀጣናን ለማሳደግ ቁልፍ ሚናን እንደሚጫወት ፖል ካጋሜ መግለፃቸውን ቻይና ዴይሊ ዘግቧል።
በሜሮን ንብረት