Search

የሀገር መከላከያ ሠራዊት ከምን ጊዜውም በላይ ድንቅ ብቃት ላይ ነው - ፊልድ ማርሻል ብርሃኑ ጁላ

ሰኞ ሐምሌ 14, 2017 856

የሀገር መከላከያ ሠራዊት ከምን ጊዜውም በላይ በድንቅ ብቃት ላይ መሆኑን የጦር ኃይሎች ጠቅላይ ኢታማዦር ሹም ፊልድ ማርሻል ብርሃኑ ጁላ ገለጹ።
ሠራዊቱ ዘውትር ዝግጅት ያደርጋል ያሉት ኢታማዦር ሹሙ፣ "ሆኖም ዝግጅታችን በየአከባቢው ተሰንቅረው ላሉ ትናንሽ ታጣቂ ቡድኖች አይደለም፤ አቅማችን ከዚያ በላይ ነው" ሲሉ አክለዋል።
በሀገሪቱ በተለያዩ ክፍሎች ያሉ ታጣቂ ኃይሎች መንግሥት እያቀረበ ያለውን የሰላም ጥሪ እንዲቀበሉ እና ትጥቃቸውን በመፍታት ለሀገር ብልፅግና የበኩላቸውን እንዲወጡም ጥሪ አቅርበዋል።
ባለፉት ዓመታት በሀገሪቱ የፀና ሰላምን ለማምጣት መንግሥት በሆደ ሰፊነት በተለያዩ አማራጮች የሰላም ጥሪ ሲያቀርብ መቆየቱን አስታውሰዋል።
 
በራሔል አብደላ