የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ለ7ኛው ጠቅላላ ምርጫ የተዘጋጀውን "ምርጫችን ነው - ሀገር ያለኛ" የተሰኘ ሕብረ ዜማ አስመርቋል።
መዝሙሩ በምርጫ ሂደት በተለያዩ ምክንያቶች የተገለሉ የኅብረተሰብ ክፍሎች ተሳትፎ እንዲያድግ፣ ዜጎች መብትና ግዴታቸውን አውቀው በንቃት እንዲሳተፉ እና አገራዊ አንድነት እንዲጎለብት ያለመ መሆኑ ተገልጿል።
የቦርዱ ሰብሳቢ ወይዘሮ ሜላትወርቅ ኃይሉ ሕብረ ዜማው ሁሉንም የኅብረተሰብ ክፍል የሚያሳታፍ በመሆኑ፣ መገናኛ ብዙኃን ለሕዝቡ ተደራሽ እንዲያደርጉት አሳስበዋል።
ሰብሳቢዋ አክለውም በእጩዎች ምዝገባ መርሃ ግብር በርካታ ዕጩዎች መመዝገባቸውን ጠቅሰው፣ ከየካቲት 28 ቀን 2018 ዓ.ም ጀምሮ በኢትዮጵያ ለመጀመሪያ ጊዜ በመደበኛና በዲጂታል መንገድ የመራጮች ምዝገባ እንደሚጀመር አስታውቀዋል።
ለዚህም ይረዳ ዘንድ አስፈላጊው ሥልጠናና የግብዓት ማጓጓዝ ሥራ መጀመሩን ገልፀዋል።
ምርጫው ነፃ፣ ፍትሐዊና ዲሞክራሲያዊ ሆኖ እንዲጠናቀቅ ሁሉም ባለድርሻ አካላት የበኩላቸውን እንዲወጡ ወይዘሮ ሜላትወርቅ ጥሪ አቅርበዋል።
በፍሬህይወት ረታ
#EthiopianBroadcastingCorporation #Ethiopia #ምርጫ2018 #election #NEBE