ፅናት የሚመነጨው ከሀገር ፍቅር ነው ሲሉ የመከላከያ ሚኒስቴር አመራሮች ገለጹ።
"ሀገር ከሌለ ማንም ሰው ክብር የለውም" ያሉት የኢ.ፌ.ዴ.ሪ መከላከያ ሚኒስቴር የልዩ ዘመቻዎች አዛዥ ሌ/ጄ ሹማ አብደታ፤ ሀገርን መጠበቅ ደግሞ ፅናትን ይጠይቃል ሲሉ ገልጸዋል።
ጀግኖች አባቶቻችን በባዶ እግራቸው ተጉዘው ዓድዋ ላይ ያን ታላቅ ድል ያስመዘገቡት ፅናት ስለነበራቸው ነው ብለዋል ሌ/ጄ ሹማ ከኢቲቪ ጋር በነበራቸው ቆይታ።
ኢትዮጵያ ያሏት ጠባቂዎች ህዝቧ፣ ወታደሩ እና ፖሊስ ሠራዊቱ እንደሆኑ የጠቀሱት የኢ.ፌ.ዴ.ሪ መከላከያ ሚኒስቴር ዋር ኮሌጅ ዋና አዛዥ ብ/ጄ ቡልቲ ታደሰ በበኩላቸው፥ ወታደር እና ፖሊስ በፅናት ሀገራቸውን እንዲጠብቁ ሀገር ወዳድ መሆን አለባቸው ብለዋል።
ሀገሩን የሚወድ በፅናት ይኖራል፤ ለሀገሩ መከፈል ያለበትን እስከ ሕይወት መስዋዕትነት የሚደርስ ዋጋም በፅናት ይከፍላል ነው ያሉት።
ኢትዮጵያ በተለያዩ ጊዜያት ከውጭም ከውስጥም ችግሮች በገጠሟት ጊዜ ወታደሮቿ በቁርጠኝነት፣ በፅናት እና በአይበገሬነት የሀገራቸውን ክብር እና ሉዓላዊነት ጠብቀዋል ብለዋል።
በሜሮን ንብረት
#EBCdotstream #ETV #Ethiopia #ENDF #resilience #የፅናትቀን