የጦር ኃይሎች ጠቅላይ ኤታማዦር ሹም ፊልድ ማርሻል ብርሃኑ ጁላ በዛሬው ዕለት የመልካ ቃሊቲ የሎጂስቲክስ ማዕከልን ዛሬ መርቀው ከፍተዋል።
ማዕከሉ ደረጃውን የጠበቀ የውስጥ ለውስጥ አስፓልት መንገድ፣ የኳስ ሜዳ፣ የመዝናኛ ክበብ እና ሌሎች አስፈላጊ መሠረተ ልማቶች የተሟሉለት ነው።
የመከላከያ ሎጂስቲክስ ዋና መምሪያ ኃላፊ ሌተናል ጄኔራል አብዱራህማን እስማኤል በምረቃው ወቅት፥ ማዕከሉ የሎጂስቲክስ አቅርቦት ማከማቻ መሆኑን አስረድተዋል።
ማዕከሉ ከዚህ ቀደም ለስራ ምቹ እንዳልነበረ አስታውሰው፤ አሁን በአመራሩ ቁርጠኝነት ፅዱና ለሥራ ምቹ አካባቢ መፍጠር መቻሉን ገልጸዋል።
ከጦር ኃይሎች ጠቅላይ ኤታማዦር ሹም ፊልድ ማርሻል ብርሃኑ ጁላ በተጨማሪ የጦር ኃይሎች ምክትል ጠቅላይ ኤታማዦር ሹም ጀኔራል አበባው ታደሰ፣ ጀነራል መኮንኖች እንዲሁም የዕዝ፣ የኮር እና የክፍለጦር አመራሮች በምረቃ ሥነ-ሥርዓቱ ላይ ተገኝተዋል።
#EBCdotstream #DefenseForce #LogisticsCenter