የኅብር ቀን በአፋር ክልል ሰመራ ከተማ "ብዝሃነት የኢትዮጵያ ጌጥ" በሚል መሪ ሃሳብ በተለያዩ መርሃ-ግብሮች እየተከበረ ይገኛል።
የሰመራ ከተማ ነዋሪዎች ፣ ወጣቶች ፣ የመንግሥት ሰራተኞች እና ከፍተኛ የመንግሥት የሥራ ሃላፊዎች በተገኙበት የመንገድ ላይ ትርዒቶች ቀርበዋል።
ኢትዮጵያውያን በዐድዋ ድል፣ በታላቁ የሕዳሴ ግድብ እና በተለያዩ የልማት መስኮች ላይ ያሳዩትን ሕብረት የሚያወሱ ሁነቶችም ተካሂደዋል።
የኅብር ቀንን አስመልክቶ ለአቅመ ደካሞች የማዕድ ማጋራት መርሃ-ግብር ተከናውኗል።
#EBC #ebcdotstream #Unity #Afar