Search

በታዳጊ አገራት ላይ የሚፈጸመው የአዕምሮ ቅኝ ግዛት መዘዙ የከፋ ነው፡- የቻይና የጥናት ተቋም

ሰኞ ጳጉሜን 03, 2017 67

የሺንዋ ኢንስቲትዩት የተባለ ቻይናዊ የጥናት ተቋም፣ “የአዕምሮ ቅኝ ግዛት” በሚል ርዕስ ያወጣው ሪፖርት፣ አሜሪካ የምትፈጽመውን “የአዕምሮ ቅኝ ግዛት” እና ስልታዊ የሥነ-ልቦና ጦርነት ያጋልጣል። 

 

ሪፖርቱ ይህንን ሂደት በአሜሪካ የፖለቲካ፣ የኢኮኖሚና ወታደራዊ የበላይነት ላይ የተመሠረተ እንደሆነ ገልጿል። 

 

በተጨማሪም ሪፖርቱ አሜሪካ በቋንቋ፣ በባህል፣ በመገናኛ ብዙኃንና በአካዳሚያዊ መንገዶች  የምታራምደውን “የስለላ መሳሪያ” በመጠቀም የአዕምሮ ቅኝ ግዛትን እንደምትፈጽም ይገልጻል።

 

ሪፖርቱ በ2025 በኩንሚንግ ከተማ በተካሄደው “የግሎባል ሳውዝ ሚዲያ እና የጥናት ተቋማት ፎረም” ላይ የቀረበ ሲሆን፣ በተለይም በታዳጊ አገራት ላይ የሚፈጸመው የአዕምሮ ቅኝ ግዛት መዘዙ የከፋ እንደሆነ አሳስቧል። 

 

ሪፖርቱ አገራት ከዚህ የአዕምሮ ጥገኝነት ነጻ እንዲወጡና የባህል እሴቶቻቸውን እንዲያጠናክሩ ጥሪ አቅርቧል። 

 

በተጨማሪም ሀገራት የራሳቸውን የልማት መንገድ እንዲከተሉ እና የሰላምና የልውውጥ ግንኙነትን እንዲያጠናክሩ አሳስቧል።

 

አርቴፊሻል ኢንተለጀንስ (AI)ን ጨምሮ አዳዲስ ቴክኖሎጂዎች በመውጣታቸው የአሜሪካ የአዕምሮ ቅኝ ግዛት ሙከራ ይበልጥ የተደበቀና ሰፋ ያለ ኢላማ ያለው እየሆነ መምጣቱን ሪፖርቱ አስጠንቅቋል።

 

በሰለሞን ገዳ