የቻይናው ፕሬዝዳንት ዢ ጂንፒንግ በበይነ መረብ በተካሔደ የብሪክስ የመሪዎች ስብሰባ ላይ እንደተናገሩት፣ ቻይና በቤልት ኤንድ ሮድ ኢኒሼቲቭ ማዕቀፍ ውስጥ ከብሪክስ ሀገራት ጋር ከፍተኛ ጥራት ያለው ትብብር ለማስፋፋት ዝግጁ ነች።
ስብሰባው በብራዚል ፕሬዝዳንት ሉዊዝ ኢናሲዮ ሉላ ዳ ሲልቫ የተጠራ ሲሆን፣ በአሜሪካ ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ የንግድ ፖሊሲ ላይ ለመወያየት ያለመ ነው።
የቻይና የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ፕሬዝዳንት ዢ “ቻይና ከብሪክስ አባል ሀገራት ጋር በመተባበር የዓለም አቀፍ የልማት ኢኒሼቲቭን እና ከፍተኛ ጥራት ያለውን የቤልት ኤንድ ሮድ ትብብርን ለማስፋፋት ዝግጁ ናት” ብሏል።
የቤልት ኤንድ ሮድ ኢኒሼቲቭ በቻይና በአውሮፓውያኑ አቆጣጠር በ2013 የተጀመረ ዓለም አቀፍ የመሠረተ ልማት ግንባታ ፕሮጀክት ነው።
በጥንታዊው የሐር መንገድ (Silk Road) መሰረት አድርጎ የተዘጋጀ ሲሆን ፤ ይህ ፕሮጀክት ቻይናን በየብስ ከማዕከላዊ እስያ፣ ሩሲያ እና አውሮፓ ጋር፤ በባህር ደግሞ ከደቡብ ምሥራቅ እስያ፣ መካከለኛው ምስራቅ፣ አፍሪካ እና ላቲን አሜሪካ ጋር ለማገናኘት ያለመ ነው።
በአሁኑ ጊዜ ከ150 በላይ ሀገራትንም በአውሮፓውያኑ አቆጣጠር በ2006 የተመሰረተው ብሪክስ የመንግስታት ትብብር ማእቀፍ ነው።
ከመሥራች ሀገራት ብራዚል፣ ሩሲያ፣ ህንድ፣ ቻይና እና ደቡብ አፍሪካ በተጨማሪ አሁን ኢትዮጵያ፣ ኢራን፣ ግብጽ፣ ኢንዶኔዢያ እና የተባበሩት አረብ ኤሚሬቶች አባላት ናቸው።
ማሌዢያ፣ ቤላሩስ፣ ቦሊቪያ፣ ካዛኪስታን፣ ታይላንድ፣ ኩባ፣ ኡጋንዳ፣ ናይጄሪያ፣ ኡዝቤኪስታን እና ቬትናም ደግሞ የብሪክስ አጋር ሀገራት ናቸው።
በሰለሞን ገዳ