Search

የኢትዮጵያውያን የመቻል ምልክቱ ታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ ተመረቀ

ማክሰኞ ጳጉሜን 04, 2017 194

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/

የኢትዮጵያውያን የመቻል ምልክት የሆነው ታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብን ከሌሎች ጥሪ ከተደረገላቸው መሪዎች ጋር በይፋ መርቀዋል።

የአፍሪካ እና ካሪቢያን መሪዎች ተወካዮቻቸው በግድቡ ምረቃ ላይ ተገኝተው የኢትዮጵያን ደስታ ተካፍለዋል።

 

የአፍሪካውያን የጋራ ትዕምርት በሆነው በታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ ምረቃ ሥነ-ሥርዓት ላይ የጂቡቲው ፕሬዚዳንት ኦማር ጌሌ፣ የደቡብ ሱዳን ፕሬዚዳንት ሳልቫ ኪር፣ የሶማሊያው ፕሬዚዳንት ሀሰን ሼክ መሐሙድ፣ የኬንያው ፕሬዚዳንት ዊሊያም ሩቶ፣ የባርቤዶሷ ጠቅላይ ሚኒስትር ሚያ ሞትሊ፣ የስዋቲኒ ጠቅላይ ሚኒስትር ሚሶ ድላሚኒ እንዲሁም የአፍሪካ ኅብረት ኮሚሽን ሊቀመንበር ማሕሙድ ዓሊ ዩሱፍ እና የተመድ ምክትል ዋና ጸሐፊ እና በተመድ የአፍሪካ ኢኮኖሚክ ኮሚሽን ዋና ሥራ አስፈፃሚ ክላቨር ጋቴቴ ተገኝተዋል።

በለሚ ታደሰ