ለሠራነው ገድል ሳይሆን ከፊታችን ላለው ከባድ ሥራ ታጥቀን እንነሳ ሲሉ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) መልዕክት አስተላለፉ።
ጠቅላይ ሚኒስትሩ በሕዳሴ ግድብ ምርቃት ላይ ባስተላለፉት መልዕክት “የኢትዮጵያን ብልፅግና እና ዕድገት ለማፋጠን ጊዜው ነግቷል፤ ሳይመሽብን ሥራችንን እንድንጨርስ በጋራ አብረን እንድንቆም እጠይቃለሁ” ብለዋል።
የኢትዮጵያ የታሪክ እጥፋት፣የብልፅግና መሰረት እና የማንሰራራት ዘመን ዛሬ በሁሉም የኢትዮጵያ አቅጣጫ ታውጇልም ብለዋል ጠቅላይ ሚኒስትሩ።
ስለሆነም ኢትዮጵያዊያን ሳይረፍድብን ተባብረን እና ተደምረን ኢትዮጵያን ልናቀናት ይገባልም ነው ያሉት።
በሰለሞን ከበደ