Search

ኢትዮጵያ የኒውክሌር ማበልጸጊያ ግንባታ በቅርቡ ትጀምራለች - ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር)

ማክሰኞ ጳጉሜን 04, 2017 72

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (/) ኢትዮጵያ ከሕዳሴ ግድብ የሚስተካከል ለሰላማዊ አገልግሎት የሚውል የኒውክሌር ማበልጸጊያ ግንባታ በቅርቡ እንደምትጀምር ገለጹ።

ከዚህ ባለፈ በአፍሪካ ግዙፍ የሆነውን የኢትዮጵያ አየር መንገድ ግንባታ በቅርቡ ይጀመራልም ብለዋል።

በጥቂት ሳምንታት ውስጥ ደግሞ የመጀመሪያው የጋዝ ፋብሪካም ይመረቃል፤ በዛው ዕለት ሁለተኛው እና ከመጀመሪያው 10 እጥፍ የሚበልጠው ሁለተኛው የጋዝ ፋብሪካ ግንባታ ይጀመራልም ነው ያሉት ጠቅላይ ሚኒስትሩ።

በዛው ሰሞን የኢትዮጵያን የረጅም ዘመን ነዳጅ የማውጣት ፍላጎት እውን የሚያደርገው የንዳጅ ማጣሪያ እውን እንደሚሆንም ጠቁመዋል።

በቅርቡ የተፈረመው የማዳበሪያ ፋብሪካ ግንባታም በቀጣይ ጥቂት ጊዜያት እውን እንደሚሆን ገልጸዋል።

በሚቀጥሉት 5 ወይም 6 ዓመታት በትንሹ 1.5 ሚሊየን በላይ ቤቶች ይገነባሉም ነው ያሉት ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ።

በድምሩ 30 ቢሊየን ዶላር በላይ ሃብት የሚፈስስባቸው እና የአፍሪካን ልጆች ቀና የሚያደርጉ፤ የኢትዮጵያን ብልጽግና የሚያረጋግጡ ሜጋ ፕሮጀክቶች እንደሚገነቡም ተናግረዋል።

ከዚህ በኋላ ስለሠራነው ገድል ለማውራት ሳይሆን ወደፊት ስለሚጠብቁን ከባድ ሥራዎች ዝግጁ እንድሆን እጠይቃለሁም ሲሉም አፅንኦት ሰጥተዋል።

የኢትዮጵያ የማንሰራራት ጊዜ ዛሬ በኢትዮጵያ ሁሉም አቅጣጫዎች ታውጇል፤ ሁላችንም ተባብረን ይህን እውን እናድርገው ሌላውን ሁሉም ስለሞከርን በዚህኛው መንገድ እንጓዝም ብለዋል።

በሰለሞን ከበደ