ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በሕዳሴ ግድብ ምረቃ ወቅት፤ “ታሪክ ሰምተናል ታሪክ አይተናል ታሪክ ተምረናል ዛሬ ፈጣሪ የመረጠው ትውልድ ስለሆንን ታሪክ ሰርተናል” ብለዋል።
ሕዳሴ ለኢትዮጵያዊያን ብቻ ሳይሆን ለጥቁር ሕዝቦች ሁሉ ምድር እስክትሰበሰብ ታሪክ ሆኖም ይኖራል ብለዋል።
መላ ኢትዮጵያዊያን በየትኛውም አመለካከት ውስጥ ቢሆኑ ይህን ሳያዩ እንዳያልፉ ነው ፀሎቴ ያሉት ጠቅላይ ሚኒስትሩ፤ ሁሉም የትውልዱን ገድል መጥቶ እንዲመለከት ጋብዘዋል።
ግድቡ ከኢትዮጵያዊያን አልፎ የጥቁሮችን መቻል ማሳያ መሆኑንም ጠቅሰው፤ የመቻል የመቀጠል ምልክታችንን መጥታችሁ እንድትመለከቱ ግብዣዬ ነው ብለዋል ጠቅላይ ሚኒስትሩ።
ዳግማዊ የዓድዋ ድል ተምሳሌት በጉባ ላይ በትውልዱ በመሰራቱ የኢትዮጵያ የልመና፣ የስንፍና እና የእንጉርጉሮ ታሪክ አብቅቶ፤ኢትዮጵያ በልኳ የምትታይበት ብልፅግናዋ የሚገለጥበት ሆኗል ብለዋል።
ኢትዮጵያ ትበለፅጋለች፣ ኢትዮጵያ ከተረጂነት ወጥታ ረጂ ትሆናለችም ብለው፥ ኢትዮጵያ ከራሷ አልፋ ለወዳጆቿ ከሃብቷም ከእውቀቷም የምታካፍል ሀገር ትሆናለች ሲሉም ነቅ ቃል የገቡት።
በሰለሞን ከበደ