Search

የታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ መመረቅን አስመልክቶ ዓለም አቀፍ ሚዲያዎች ከዘገቡት

ማክሰኞ ጳጉሜን 04, 2017 516

ብሉምበርግ፦ አስደናቂ የምሕንድስና ስኬት የሆነው ታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ፣ የቤቶች እና የኢንዱስትሪዎች የኃይል አቅርቦትን በመሸፈን የኢትዮጵያ ኢኮኖሚያዊ ተስፋ ከፍ ያደርጋል።

ሮይተርስ፦ ታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ በአፍሪካ ትልቁ የውኃ ኃይል ፕሮጀክት ሲሆን፤ በሚሊዮኖች ለሚቆጠሩ ኢትዮጵያውያን የኤሌክትሪክ ፍላጎትን ያሟላል።

አልጀዚራ፦ ለግንባታው 5 ቢሊዮን ዶላር ወጪ የወጣበት ታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ የኢትዮጵያን የመሠረተ ልማት ልህቀት እና የአፍሪካን ትልቅ የኃይል አቅም ያሳያል።

ዶቼቬለ፦ ታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ የኢትዮጵያን የኤሌትሪክ ኃይል አቅም በእጥፍ ከማሳደጉም በላይ በምሥራቅ ሱዳን በየጊዜው የሚደርሰውን የጎርፍ አደጋ በመከላከል ለአካባቢው መረጋጋትን ያመጣል።

ሲኤንኤን፦ ከመንግሥት በተገኘ ገንዘብ፣ ከቦንድ ሽያጭ እና ከዜጎች በተሰበሰበ መዋጮ የተገነባው ታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ ሀገራዊ አንድነትን እና የፋይናንስ ነፃነትን የሚያንፀባርቅ ግዙፍ ፕሮጀክት ነው።

ቢቢሲ፦ ታላቁ የሕዳሴ ግድብ ኢትዮጵያውያንን አንድ አድርጎ የባለቤትነት ስሜትን በማጎናፀፍ ብሔራዊ ኩራትን ፈጥሯል።

አሶሼትድ ፕሬስ፦ ከ5 ሺህ ሜጋ ዋት በላይ የኤሌትሪክ ኃይል ማመንጨት የሚችለው ታላቁ የሕዳሴ ግድብ የኢትዮጵያን የኤሌትሪክ ኃይል አቅም በእጥፍ ከማሳደግ ባሻገር ለአካባቢው ሀገራት የኤሌትሪክ ኃይል እያቀረበ ነው።

ዘ-ኢኮኖሚስት፦ ታላቁ የሕዳሴ ግድብ ኢትዮጵያን በአካባቢው ለሚገኙ ሀገራት የኃይል ማዕከል በማድረግ የኢኮኖሚ ዕድገትን ያፋጥናል።

ዘ-ኮንቨርሴሽን፣ ታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ በቀጣናው ላሉ ሀገራት ቀዳሚ የኃይል ምንጭ በመሆን ልማትን ያሳድጋል።

ኤቢሲ ኒውስ፣ ታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ በሚሊዮን ለሚቆጠሩ ኢትዮጵያውያን የአስተማማኝ የኤሌትሪክ ኃይልና የኢኮኖሚያዊ ዕድገት ተስፋን የሚፈጥር ትልቅ ፕሮጀክት ነው።

ሲቢኤስ ኒውስ፣ ታላቁ የሕዳሴ ግድብ የኢትዮጵያን የኃይል አቅርቦት ከማሳደግ በተጨማሪ ዘላቂ ልማትን በማገዝ ረገድ ቀጣናዊ ፋይዳው የጎላ ነው።

አል-አረቢያ፣ ታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ በሚሊዮን ለሚቆጠሩ ሰዎች ወሳኝ የኤሌትሪክ ኃይል በማቅረብ ኢትዮጵያ በአፍሪካ የመሰረተ ልማት ዝርጋታ ላይ ያላትን መሪነት ያሳያል።

አፍሪካን ኒውስ፣ ታላቁ የሕዳሴ ግድብ ከ100 ሚሊዮን በላይ የሚሆኑ ኢትዮጵያውያንን እና ጎረቤት ሀገራትን ተጠቃሚ በማድረግ ቀጣናዊ ትብብርን ያበረታታል።

ፍራንስ24፣ በሚሊዮኖች ለሚቆጠሩ ቤቶች የኤሌክትሪክ ኃይል ለማቅረብ ዓላማ ያለው ታላቁ የሕዳሴ ግድብ ለኢትዮጵያውያን የዘመናዊ ልማት ራዕይ የማዕዘን ድንጋይ ነው።

በዋሲሁን ተስፋዬ

#Ethiopia #GERD #Unveiling #Media