Search

በእርግጥም የዛሬው ቀን ለኢትዮጵያ ታሪካዊ ቀን ነው - የአፍሪካ ሕብረት ኮሚሽን ሊቀመንበር መሐሙድ አሊ ዩሱፍ

ማክሰኞ ጳጉሜን 04, 2017 35

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በሰጡት ቁርጠኛ አመራር ታላቁ የሕዳሴ ግድብ ለምረቃ በመብቃቱ ኢትዮጵያ እንኳን ደስ አላችሁ ሲሉ የአፍሪካ ሕብረት ኮሚሽን ሊቀመንበር ገለጹ።

ሊቀመንበሩ መሐሙድ አሊ ዩሱፍ በታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ የምረቃ ሥነ-ሥርዓት ላይ ባደረጉት ንግግር በእርግጥም ይህ የዛሬው ቀን ለኢትዮጵያ ታሪካዊ ቀን ነው ብለዋል።

ኢትዮጵያውያን ካላቸው በመቆጠብና ቦንድ በመግዛት ከዓመታት ልፋትና ውጣ ወረድ በኋላ ግድቡን በደምና በላባቸው እውን ማድረግ መቻላቸውን አንስተው፤ ይህ ለትውልዱ አኩሪ ታሪክ ነው ብለዋል።

ታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ ከ5 ሺህ ሜጋ ዋት በላይ የኤሌክትሪክ ኃይል እንደሚያመነጭ የጠቀሱት ሊቀመንበሩ፤ ይህም ለኢትዮጵያ ህዝብና ለጎረቤት ሀገራት ትልቅ ፋይዳ ያለው ነው ብለዋል።

በሕዳሴው ግድብ ዙሪያ ያሉ አለመግባባቶችን ለመፍታት ሲካሄድ የነበረው የሶስትዮሽ ንግግር እንዲቀጥል ጠይቀው፤ አፍሪካውያን ማንም ጣልቃ ሳይገባብን ለችግሮቻችን አፍሪካዊ መፍትሄ የማበጀት የቀየ ልምድና ተሞክሮ አለን ብለዋል።

የሶስትዮሽ ንግግሩ እንዲቀጥልም የአፍሪካ ህብረት ኮሚሽን አስፈላጊውን ድጋፍ እንደሚያደርግ ተናግረዋል።

በመሀመድ ፊጣሞ

#Ethiopia #GERD #Inauguration