በታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ ምርቃት ላይ የተገኙት የኢስዋቲኒው ጠቅላይ ሚኒስትር ሩሴል ድላሚኒ ባደረጉት ንግግር፥ በግድብ እንደተደመሙ ገልጸው፤ በዚሕ ድንቅ የምሕድስና ውጤት ላይ የታየው በሳል የአመራር ጥበብ ለመላው አፍሪካ ምሳሌ የሚሆን ነው ብለዋል።
ኢትዮጵያ እና ሕዝቦቿ ለአፍሪካ ኩራት የሆነ ታላቅ ፕሮጀክት ሰርታችሁ አሳይታችኋል፣ ለዚሕም ታላቅ ምስጋና ይገባችኋል፤ የተሰራው ሥራ ለዚሕ ምስክር ነው፣ አፍ አውጥቶ የሚናገር ሥራ ነው ሲሉ ግድቡን ገልጸውታል።
እኔን ጨምሮ መላው የኢስዋቲኒ ሕዝቦች ከጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በሳል አመራር እና ከመላው የኢትዮጵያ ሕዝብ አንድነት የምንወስደው ብዙ ትምህርት ይኖራልም ብለዋል።
በሀብተሚካኤል ክፍሉ
#Ethiopia #GERD #Inauguration