ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) የደቡብ ሱዳን ፕሬዚዳንት ሳልቫ ኪር ማያርድትን በጽሕፈት ቤታቸው ተቀብለው በሁለትዮሽ ጉዳዮች ላይ መወያየታቸውን ገለጹ።

ጠቅላይ ሚኒስትሩ በማኅበራዊ ትሥሥር ገጻቸው ባሰፈሩት መልዕክት፣ “በሁለቱ ሀገሮቻችን ትብብራችንን ለማጠናከር እና የጋራ ቅድሚያ የምንሰጣቸው ጉዳዮችንም ተመልክተናል” ብለዋል።

የደቡብ ሱዳኑ ፕሬዚዳንት ሳልቫ ኪር በትናንትናው ዕለት በተካሄደው የታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ የምረቃ ሥነ-ሥርዓት ላይ ከታደሙ መሪዎች መካከል አንዱ ነበሩ።