Search

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ከሶማሊያ ፕሬዚዳንት ሀሰን ሼህ መሃሙድ ጋር ተወያዩ

ረቡዕ ጳጉሜን 05, 2017 42

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ዛሬ ጠዋት የሶማሊያ ፌዴራል ሪፐብሊክ ፕሬዚዳንት ሀሰን ሼህ መሃሙድን አግኝተው የጋራ ፍላጎት ባላቸው ቀጠናዊ ጉዳዮች ላይ መወያየታቸውን ገለጹ።
 
ጠቅላይ ሚኒስትሩ በማኅበራዊ ትሥሥር ገጻቸው ባሰፈሩት መልዕክት፣ “በቀጠናችን ፀጥታ እና መረጋጋት ብሎም ልማትን ለማረጋገጥ ያለንን ፅኑ አቋም በድጋሜ አረጋግጠናል” ብለዋል።