የመንግሥት አገልግሎት አሰጣጥ ሥርዓቱን የጠበቀ እና ቀልጣፋ እንዲሆን በቁርጠኝነት መስራታችንን ቀጥለናል ሲሉ የአዲስ አበባ ከንቲባ አዳነች አቤቤ አስታወቁ።
ዛሬ ጠቅላይ ሚንስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በተገኙበት "አዲስ መሶብ "የአንድ ማዕከል አገልግሎትን ሥራ አስጀምረናል ብለዋል ከንቲባዋ።
በአዲሱ ዓመት ዋዜማ አዲስ-መሶብን እነሆ ገፀ በረከት ብለናል ሲሉ ከንቲባ አዳነች በማኅበራዊ የትስስር ገፃቸው አስፍረዋል።
በ13 ተቋማት በ107 የከተማ አስተዳደር አገልግሎቶችን የሚሰጠው አዲስ መሶብ የአንድ ማዕከል የነዋዎቻችን እንግልት የሚቀንስ ፣ ቀልጣፋና ፈጣን አገልግሎት ለመስጠት አዲስ ብስራት ይዘን መጥተናል ብለዋል።
በአዲሱ ዓመት በብዙ ብርታት እና ትጋት ልናገለግላችሁ ቆመናል ሲሉምም ገልጸዋል።
#EBC #ebcdotstream #Addis Abvaba #Mesob