Search

ኢትዮጵያ በምግብ እና ሥርዓተ ምግብ ስትራቴጂ ላይ አበረታች ሥራ እየሠራች ነው - CIFF

ረቡዕ ጳጉሜን 05, 2017 59

ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ጥሩነህ ዛሬ ከችልድረን ኢንቨስትመንት ፈንድ ፋውንዴሽን (CIFF) መሥራች እና የቦርድ ሊቀመንበር ሰር ክሪስቶፈር ሆን ጋር ውይይት አድርገዋል።

ኢትዮጵያ በምግብ እና ሥርዓተ ምግብ ስትራቴጂ፣ በሰቆጣ ቃል ኪዳን፣ በግሪን ኢነርጂ፣ በእናቶች፣ በሴቶች እና በሕፃናት ጤና ላይ እየሠራች ያለው ሥራ የሚበረታታ መሆኑን ሰር ክሪስቶፈር ሆን መግለጻቸውን ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትሩ ጠቁመዋል።

በእነዚህ ጉዳዮች ላይ ድጋፋቸውን አጠናክረው እንደሚቀጥሉ ሊቀመንበሩ ቃል መግባታቸውን ነው የገለጹት።

ችልድረን ኢንቨስትመንት ፈንድ ፋውንዴሽን (CIFF) ሕዝብን ተጠቃሚ የሚያደርጉ በተለይ በንፁህ ውኃ አቅርቦት እና በሴቶች የሥራ ዕድል ፈጠራ ላይም የመሥራት ፍላጎት እንዳለው ገልጸዋል ብለዋል።

በተጨማሪም ሊቀ መንበሩ ኢትዮጵያ እየሄደችበት የምትገኝበት ሀገር በቀል ኢኮኖሚ ሪፎርም በዕጅጉ እንዳስደነቃቸው መናገራቸውን ምክትል ሚኒስትር ተመስገን ጥሩነህ በማኅበራዊ ትሥሥር ገጻቸው ባሰፈሩት መልዕክት ገልጸዋል።

#EBC #ebcdotstream #CIFF