የድሬዳዋ አስተዳደር ከንቲባ አቶ ከድር ጁሃር ለ2018 ዓ.ም አዲስ ዓመት የእንኳን አደረሳችሁ መልዕክት አስተላልፈዋል።
አቶ ከድር በመልዕክታቸው፣ አዲሱ ዘመን የመላው ኢትጵያውያን የዘመናት ቁጭት የነበረው ታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ ተጠናቅቆ ለምረቃ በመብቃቱ ድርብ የአዲስ ዘመን እና የአዲስ ምዕራፍ ብስራት ነው ብለዋል።
በአዲሱ ዘመን እንደ አስተዳደር በ2017 ዓ.ም የነበሩ ክፍተቶችን በመሙላት ለበለጠ ስኬት የምንተጋበት ነው ሲሉም አክለዋል።
በዓሉ ሲከበር የድሬዳዋ ነዋሪዎች የተለመደውን የመረዳዳት እና የመደጋገፍ ነባር ዕሴት በማጎልበት መሆን እንዳለበት ተናግረዋል።
ነዋሪው በዓሉን ያለውን በማካፈል፣ ሕሙማንን በመጠየቅ፣ የታረዙትን በማልበስ እና አቅመ ደካሞችን በማገዝ ይሆን ዘንድ ጥሪ አቅርበዋል።
አዲሱ 2018 ዓ.ም የሰላም፣ የጤና የብልፅግና እና የመመንደግ ዓመት እንዲሆን መልካም ምኞታቸውን አስተላልፈዋል።