በዲጂታል ኢትዮጵያ 2030 ስትራቴጂ፣ የ5ጂ ኔትወርክ ሽፋንን 100 ፐርሰንት ለማድረስ ይሠራል ሲሉ የኢትዮ ቴሌኮም ዋና ሥራ አስፈጻሚ ፍሬሕይወት ታምሩ ገለጹ።
ዲጂታል ኢትዮጵያ 2025 በቴሌኮም ዘርፍ በርካታ ውጤቶች የተመዘገቡበት ነው ያሉት ዋና ሥራ አስፈጻሚዋ፤ የሞባይል ደንበኞች ቁጥርን 97 ሚሊዮን ማድረስ የተቻለ በአብነት አንስተዋል።
ከእነዚህ ደንበኞች ውስጥ 57 ሚሊዮኑ የኢንተርኔት ተጠቃሚዎች መሆናቸውን ጠቅሰው፤ በተጨማሪም 1 ሺህ 30 ከተሞች የ4ጂ ኔትወርክ ተደራሽ መሆናቸውን ገልጸዋል።
ዛሬ ይፋ በሆነው ዲጂታል ኢትዮጵያ 2030 ስትራቴጂ ደግሞ የሞባይል ተጠቃሚ ደንበኞችን ቁጥር 128 ሚሊዮን፣ የ5ጂ ኔትወርክ ሽፋንን 100 ፐርስንት ለማድረስ እንደሚሠራ አስታውቀዋል።
በ2030 የዲጂታል ክፍያን ከአጠቃላይ የሀገር ውስጥ ምርት አንጻር አሁን ካለበት ከ7 እጥፍ በላይ እንዲያድግም በልዩ ትኩረት ይሠራል ብለዋል ዋና ሥራ አስፈጻሚዋ።
#EBC #ebcdotstream #Ethiopia #DigitalEthiopia #DigitalEthiopia2030 #PMOEthiopia