ኢትዮጵያ 2030 ስትራቴጂ ሰው ተኮርና ለሁሉም ሴክተሮች ትኩረት ተሰጥቶ የሚሰራበት ነው ሲሉ በጠቅላይ ሚኒስትር ጽሕፈት ቤት የዲጂታል አማካሪ ሚሪያም አሊ ገለጹ።
አዲሱ ስትራቴጂ በዲጂታል 2025 የተመዘገቡ የዲጂታል መሰረተ ልማቶችን የማስፋፋት ሥራውን በተጨባጭ ውጤት የምናሳይበት ጭምር ነው ብለዋል።
ስትራቴጂው በግልጽ የአስተዳደር ስርዓት፣ በሚለካ ውጤት እና በተጠያቂነት ላይ ተመስርቶ በቀጣይ አምስት ዓመታት ተግባራዊ ይሆናል ብለዋል አማካሪዋ።
ለዚህ ደግሞ ሁሉም የሚመለከተው አካል የጋራ ርብርብ ማድረግ ይጠበቅበታልም ነው ያሉት።
#EBC #ebcdotstream #Ethiopia #DigitalEthiopia #DigitalEthiopia2030 #PMOEthiopia