Search

ለዜጎች እኩል እድል መፍጠር የዲጂታል ኢትዮጵያ 2030 ትልም ነው - ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር)

እሑድ ታኅሣሥ 12, 2018 56

በመላው ሀገሪቱ ያሉ ዜጎች እኩል የተጠቃሚነት እድል ያላቸው እና ተመሳሳይ አገልግሎት ማግኘት እንዲችሉ ማድረግ የዲጂታል ኢትዮጵያ 2030 ትልም ነው ሲሉ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ገለፁ፡፡

ጠቅላይ ሚኒስትሩ ይህን ያሉት ዲጂታል ኢትዮጵያ 2030 በይፋ ሲጀመር በጉዳዩ ዙሪያ በሰጡት ማብራሪያ ነው፡፡

በማብራሪያቸውም፤ በዲጂታል ኢትዮጵያ 2025 የተተገበሩ ስራዎችን በማጠናከር እና በማበልፀግ የዜጎችን ተጠቃሚነት ማረጋገጥ ይገባል ብለዋል፡፡

በመረጃ እጦት ምክንያት የትኛውም ማህበረሰብ ከተጠቃሚነት መራቅ እንደሌለበት የገለፁት ጠቅላይ ሚኒስትሩ፤ ዜጎች ይህን እንዲያገኙ ማድረግ የእቅዱ ቀዳሚ አላማ ስለመሆኑ ተናግረዋል፡፡

በተከታይነት ዜጎች ባሉ እድሎች መጠቀም የሚችሉበትን መንገድ መፍጠር ተከታይ ስለመሆኑ አመላክተዋል፡፡

በተጨማሪ በተቋማት እና በዜጎች መካከል መተማመንን መፍጠር እንደሚገባ ገልፀው፤ “ዜጎች ዲጂታል የሆነ ቁስ ኖሯቸው አመኔታ በማጣት ማይጠቀሙት ከሆነ ጥረታችን  ከከንቱ ልፋት ይሆናል“ ሲሉ አስረድተዋል፡፡

በዚህም ዜጎች የሚሰጡት ሁለንተናዊ መረጃ የተጠበቀ መሆኑን የሚያምኑበት ትስስር እንዲኖር ለማድረግ እንደሚሰራ አመላክተዋል፡፡

በአፎምያ ክብበው

#EBC #ebcdotstream #Digitalethiopia2030 #PMAbiy