Search

የኢትዮጵያን የከፍታ ጉዞ አስቀጥለን ድህነትን ታሪክ ለማድረግ ቃል የምንገባበት ዘመን ነው - ርዕሰ መስተዳዳር ሙስጠፋ ሙሁመድ

ረቡዕ ጳጉሜን 05, 2017 40

የሶማሊ ክልል ርዕሰ መስተዳዳር ሙስጠፋ ሙሁመድ ለመላው ኢትዮጵያውያን እንኳን ለ2018 አዲስ ዓመት በሰላም አደረሳችሁ ሲሉ የመልካም ምኞት መልዕክታቸውን አስተላለፉ።
የ2018 ዓ.ም ጅማሮ ለኢትዮጵያውያን፣ ለኢትዮጵያ ወዳጆች እና ለመላው አፍሪካውያን በከፍተኛ ብሥራት እና ድል የታጀበ ነው ብለዋል ርዕሰ መስተዳድሩ።
በዓሉ የታላቁ ሕዳሴ ግድብን በመረቅን ማግስት የምናከብረው እንደመሆኑ ልዩ እና ታሪካዊ ያደርገዋል ሲሉ ተናግረዋል።
በግድቡ ላይ እንደ አንድ ሆነን ያሳረፍነውን አሻራ በቀጣይ በግዙፍ ፕሮጀክቶች ላይ መድገም እንደሚገባ መልዕክት አስተላልፈዋል።
የኢትዮጵያን የከፍታ ጉዞ አስቀጥለን ድህነትን ታሪክ ለማድረግ ቃል የምንገባበት ዘመን ነው ብለዋል።
ነገ አንድ ብለን በምንቀበለው አዲስ ዓመት ብስራት እና ድሎቻችን ይበልጥ የሚያንጸባርቁበት፣ ከበረከቱ ፍሬ የምንቋደስበት፣ የኢትዮጵያ የመነሳት ደውልም ከሀገራችን አልፎ ለአህጉራችንም የሚሰማበት እንዲሆን እመኛለሁ ብለዋል።
ርዕሰ መስተዳድሩ ለመላው ኢትዮጵያውያን በሙሉ አዲሱ ዓመት የአንድነት፣ የፍቅር፣ የሰላምና የብልፅግና እንዲሆን የመልካም ምኞት መልዕክት አጋርተዋል።
በቴዎድሮስ ታደሰ