Search

ሕዳሴ ግድብ በተመረቀበት ማግስት የሚከበር አዲስ ዓመት ነው:- ሌተናል ጄኔራል ይልማ መርዳሳ 

ሓሙስ መስከረም 01, 2018 75

ሕዳሴ ግድብ በታላቅ ድምቀት ተመርቆ በይፋ ሥራ የጀመረበት መሆኑ አዲሱን ዓመት ልዩ ያደርገዋል ሲሉ የኢፌዴሪ አየር ኃይል ዋና አዛዥ ሌተናል ጄኔራል ይልማ መርዳሳ ገለጹ። 

ሌተናል ጄኔራል ይልማ ይህን ያሉት ለመላው የኢትዮጵያ ህዝቦች፣ የመከላከያ ሠራዊት አባላት እንዲሁም መላው የተቋሙ ሲቪል ሰራተኞች ባስተላለፉት የእንኳን አደረሳችሁ መልዕክት ነው። 

ዋና አዛዡ በመልዕክታቸው በተጠናቀቀው 2017 ሀገራችን በሰላም በልማት በኢኮኖሚ ዕድገትና በማህበራዊ መስኮች ታላላቅ ስኬቶችን ያስመዘገበችበት የድል ዓመት እንደነበር አንስተዋል።

አዲሱ ዓመትም መላው ኢትዮጵያዊ እና ጀግናው ሠራዊታችን ደሙን፣ ላቡን፣ ጉልበቱንና እውቀቱን ከማፍሰስ ባሻገር ቦንድ በመግዛት የራሱን ታሪካዊ አሻራ ያሳረፈበት ታላቁ የሕዳሴ ግድብ በታላቅ ድምቀት ተመርቆ በይፋ ሥራ የጀመረበት እና አየር ኃይላችንም ከተቋማዊ ሪፎርሙ ወዲህ የጀመራቸውን የለውጥ ጉዞዎች አጠናክሮ የቀጠለበት ነው ብለዋል።

 የተቋሙን የዝግጁነት አቅም ለማሳደግ ያከናወናቸው ተግባራት ከዓመቱ አመርቂ ድሎቻችን ውስጥ የሚጠቀሱ ሲሆን፤ ሠራዊታችንም የአስተሳሰብ ለውጥ በማምጣት የአመራሩንም ሆነ የአባላቱን ሥነ-ልቦና በማሳደግ የሚሰጠውን ተልዕኮ ለመወጣት የሚያስችል ቁመና እንዲይዝ ተደርጓል ነው ያሉት።

የኢትዮጵያ አየር ኃይል የተመሰረተበትን 90ኛውን አመት በተለያዩ ዝግጅቶች በድምቀት ለማክበር በዝግጅት ላይ መሆኑንም ጠቅሰው፤ አዲሱ ዓመት የተጣለብንን ሀገራዊ ኃላፊነት ከመቼውም ጊዜ በላቀ የወትሮ ዝግጁነት የምንወጣበ