አዲሱ ዓመት የኢትዮጵያውያን አንድነት፣ ብልፅግና እና ሰላም ይበልጥ የሚጠናከርበት ዓመት እንዲሆን መልካም ምኞታቸውን የአፍሪካ ሕብረት ኮሚሽን ሊቀመንበር መሀሙድ አሊ ዩሱፍ ገለፁ፡፡
የኮሚሽኑ ሊቀመንበር ለኢትዮጵያ መንግሥትና ሕዝብ እንኳን ለአዲሱ ዓመት በሰላም አደረሳችሁ ብለዋል፡፡
ሊቀመንበሩ በመልዕክታቸው "ኢትዮጵያውያን አዲሱን ዓመት ሲያከብሩ ለብልፅግና እና ዘላቂ ሰላም መረጋገጥ ቁርጠኝነታቸውን የሚያድሱበት እንዲሆን እመኛለሁ" ነው ያሉት፡፡
ኢትዮጵያውያን በአዲሱ ዓመት ለሀገራቸው ብቻ ሳይሆን ለአህጉሪቱ አንድነትና እድገት አስተዋፅኦ የሚያደርጉበት ወቅት እንዲሆን ተመኝተዋል፡፡
በላሉ ኢታላ