Search

የዘንድሮው አዲስ ዓመት ታላቁ የሕዳሴ ግድብ በተመረቀበት ማግስት የምናከብረው በመሆኑ ይለያል - ርዕሰ መስተዳድር አረጋ ከበደ

ሓሙስ መስከረም 01, 2018 61

የዘንድሮው አዲስ ዓመት ታላቁ የሕዳሴ ግድብ በተበሰረበት ማግስት የምናከብረው በመሆኑ በዓሉን ልዩ ያደርገዋል ሲሉ የአማራ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አረጋ ከበደ ገለጹ።

አቶ አረጋ ለመላው ህዝብ ባስተላለፉት የእንኳን አደረሳችሁ መልዕክታቸው፥ የሕዳሴ ግድብን በራሳችን አቅም ማጠናቀቅ መቻላችን በአንድነት ከቆምንና በጋራ ከተጋን በሁሉም አሸናፊ መሆን እንደምንችል በተግባር ያሳየንበት ነው ብለዋል።

የአዲሱ ዓመት መባቻ የሆነው የመስከረም ወርም ለአዳዲስ ስኬቶች ራሳችን የምናዘጋጅበት፤ ለዕድገትና ለለውጥ አቅደን የምንነሳበት፣ ተስፋና ምኞትን የምንሰንቅበት ነው ብለዋል ርዕሰ መስተዳድሩ።

ያለፈው ዓመት የክልሉን ሰላም ለማረጋገጥ እንዲሁም የልማት ሥራዎችን ለማከናወን በተደረገው የተቀናጀ ርብርብ አመርቂ ስኬት እንደነበር ነው አቶ አረጋ አንስተዋል።

በመጪው 2018 አዲስ ዓመትም በክልላችን ዘላቂ ሰላም በማስፈንና ልማታችንን በላቀ ደረጃ በመፈፀም የሕዝባችንን ሁለንተናዊ ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ ከፍ ባለ ቁርጠኝነት እንሠራለን ብለዋል።

አዲሱ ዓመት ለመላው የኢትዮጵያ ህዝብ የሰላም፣ የጤና፣ የፍቅር፣ የመተሳሰብ፣ የአብሮነት፣ የአንድነት እና የስኬት ዘመን እንዲሆንም ተመኝተዋል።

#EBCdotstream #Ethiopia #NewYear #2018EC