መቀመጫቸውን አዲስ አበባ ያደረጉ የተለያዩ ሀገራት አምባሳደሮች አዲሱን የኢትዮጵያውያውን ዓመት ዓመት ምክንያት በማድረግ ለመላው ህዝብ የእንኳን አደረሳችሁ መልዕክት አስተላልፈዋል።
በኢትዮጵያ የአሜሪካ አምባሳደር ኧርቪን ማሲንጋ ባስተላለፉት የአዲስ ዓመት መልካም ምኞት፥ ዓመቱ ተስፋዎችን የምናድስበት፣ የሁለቱን ሀገራት ግንኙነት የምናጠናክርበት፤ ኢትዮጵያውያን የጋራ ሰላማቸውን የሚገነቡበት እንዲሆን ተመኝተዋል።
በኢትዮጵያ የእስራኤል ኤምባሲ አዲሱ ዓመት የሰላምና የፍቅር እንዲሁም የዕድገትና የብልጽግና እንዲሆን መልካም ምኞቱን ገልጿል።
በኢትዮጵያ የካናዳ፣ የቱርክ፣ የአውስትራሊያ፣ የፈረንሳይ፣ የስዊድን፣ የእግሊዝ እና የሌሎችም ሀገራት አምባሳደሮችም አዲሱ ዓመት የሰላም፣ የደስታ እና የብልፅግና እንዲሆን መልካም ምኞታቸውንም ገልጸዋል።
በላሉ ኢታላ
#EBCdotstream #Ethiopia #NewYear #EthiopianNewYear #2018EC