በዘርፈ ብዙ ድሎች ደምቀን ለምናከብረው የ2018 አዲስ ዓመት እንኳን በሰላምና በጤና አደረሳችሁ ሲሉ የሲዳማ ክልል ርዕሰ መስተዳድር ደስታ ሌዳሞ ለመላው የኢትዮጵያ ህዝብ መልዕክት አስተላልፈዋል።
አቶ ደስታ በመልካም ምኞት መግለጫ መልዕክታቸው፥ የህብረታችንን ጥንካሬ ያስመሰከርንበትን የታላቁ የሕዳሴ ግድብ ግንባታን አጠናቀን እና አስመርቀን በሀሴት ውስጥ ሆነን አዲሱን ዘመን መቀበላችን ደስታችንን እጥፍ ድርብ አድርጎታል ብለዋል።
ግድቡ ለአንድ ዓላማ በጋራ መሰለፍ ወደ ታለመ መዳረሻና ግብ የሚያደርሰን ድልድይ መሆኑን አሳይቶናልና የሀገራችን የዕድገት ልዕልና የሚረጋግጥበት ለሆነው ህብረታችን እና አድነታችን ልዩ ክብር ልንሰጠው ይገባል ብለዋል።
አዲሱ ዓመት የሌሎች ታላላቅ ፕሮጀክቶች ግንባታን የምንጀምርበት እንዲሁም የጀመርናቸውን የምናፋጥንበት እና የምናስመርቅበት ይሆናል ያሉት ርዕሰ መስተዳድሩ፤ ለዚህ ስኬት ሁላችንም ውድና መተኪያ የሌላትን ሀገራችንን በታማኝነትና በትጋት ማገልገል ይገባናል ሲሉ መልዕክት አስተላልፈዋል።
#EBCdotstream #Ethiopia #NewYear #EthiopianNewYear #2018EC