የሲዳማ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት ርዕሰ መስተዳድር አቶ ደስታ ሌዳሞ የ2018 ዓ.ም የዘመን መለወጫ በዓልን ምክንያት በማድረግ ለ1 ሺህ 227 የሕግ ታራሚዎች ይቅርታ አደረጉ።
ርዕሰ መስተዳድሩ በክልሉ የይቅርታ ቦርድ ተጣርቶ በቀረበላቸው መሰረት ለ1 ሺህ 200 ወንድ እና ለ27 ሴት ታራሚዎች ይቅርታ አድርገዋል።
የየአካባቢው አስተዳደሮችም በይቅርታ የወጡ ዜጎችን ከማህበረሰቡ ጋር እንዲቀላቀሉ ድጋፍና ክትትል እንዲያደርጉ አሳስበዋል አቶ ደስታ።
በይቅርታ የወጡ ታራሚዎችም በቀጣይ ሕይወታቸው ከጥፋት እንዲቆጠቡ፣ ህዝባቸውን እንዲያገለግሉ እና እንዲክሱ ይጠበቃል ነው ያሉት።
#EBCdotstream #EthiopianNewYear #2018EC #Amnesty #Clemency #Pardon