በነገው የአዲስ ቀን የዜና መሰናዶ የሀገር ጉዳይ በኢትዮጵያ የሚዲያ ታሪክ ውስጥ የበኩር ድምፅ የሆነውን የኢትዮጵያ ብሔራዊ ሬዲዮን ጉዞ እንዳስሳለን።
የሀገሪቱን ታሪኮች ለዘመናት ሰንዶ ያስቀመጠው አንጋፋው የሬዲዮ ጣቢያ መስከረም 2 ቀን 2018 ዓ.ም ስርጭት ከጀመረ ድፍን 90 ዓመት ይሆነዋል።
ኢቢሲ 90 ዓመታትን በብሔራዊ ሬዲዮ ፣ 60 ዓመታት በቴሌቪዥን እንዲሁም 25 ዓመታትን ደግሞ በኤፍ ኤም አዲስ 97.1 ያስቆጠረ አንጋፋ ተቋም ነው።
አዲስ ቀን የዜና መሰናዶ ይህንን የሀገር ጉዳይ ጨምሮ ሌሎች ጥንቅሮችን አካቶ ነገ ከጠዋቱ 1:00 እስከ 3:00 ሰዓት ከነፃነት ፍቅሩ እና ከአብዮት ይግዛው ጋር ይጠብቃችኋል።
አዲስ ቀን!