Search

ሕዳሴ እያንዳንዱ አፍሪካዊ ሊጎበኘው የሚገባ ፕሮጀክት ነው - አሜሪካዊው ምሁር ላውረንስ ፍሪማን

ሓሙስ መስከረም 01, 2018 118

ታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ የሰው ልጅ ተፈጥሮን ተጠቅሞ ለተሻለ ነገር ማዋል እንደሚችል ያሳየ ጥበብ ነው ሲሉ አሜሪካዊው የፖለቲካ ተንታኝ ላውረንስ ፍሪማን ገልጸዋል።
እስካሁን ግድቡን የጎበኙ አፍሪካውያን በጣም ጥቂት መሆናቸውን አንስተው፤ አፍሪካውያንም ሆነ አውሮፓውያን ሕዳሴውን መጎብኘት እንዳለባቸውም ነው የተናገሩት።
የአፍሪካ ሕብረት እንዲሁም መላው አፍሪካውያን አይተው ሊደነቁበት እና ለሌላ የልማት ሥራ ሊነሳሱበት የሚገባ ፕሮጀክት መሆኑንም ላውረንስ ፍሪማን አመላክተዋል።
እኔ ሁለት ጊዜ ግድቡን ለመጎብኘት በመቻሌ ዕድለኛ እንደሆንኩ ይሰማኛል ያሉት የፖለቲካ ተንታኙ፤ ሌሎችም ጎብኝተው በየዘርፋቸው ሊደግሙት የሚገባ የስኬት ማሳያ መሆኑንም ገልጸዋል።
እያንዳንዱ የአፍሪካ ሀገር የኢትዮጵያን ሞዴል በመከተል የሕዝቡን የኑሮ ደረጃ ከፍ የሚያደርግ፣ የማምረቻውን ዘርፍ የሚያሳድግ፣ መስኖን የሚያስፋፋ እና ድህነትን የሚያስወግድ የኃይል አቅርቦትን መገንባት ይኖርበታል ሲሉም ተናግረዋል።
የታችኛው ተፋሰስ ሀገራት የዚህን ግድብ ስኬት የሚያንኳስሱበት ምንም ምክንያት እንደሌላቸው ጠቁመው፤ ይህ ግድብ የታችኛው ተፋሰስ ሀገራትን የውሃ ሃብት አጠቃቀም ለማሳደግ እንደሚረዳም ነው ያነሱት።
ግድቡ የመቶ ሚሊዮኖችን አፍሪካውያንን የኑሮ ደረጃ እንዴት ማሳደግ እና ድህነትን እንዴት መቀነስ እንደሚቻል ያመላከተ፤ በተጨማሪም የናይል ተፋሰስ ሀገራትን አዲስ ራዕይ ያመላከተ ግድብ ነው ሲሉም አሜሪካዊው ምሁር ላውረንስ ፍሪማን ተናግረዋል።
 
በጌትነት ተስፋማርያም