Search

ቻይና የምታስተናግደው የመከላከያ ባለስልጣናት ኮንፈረንስ

ዓርብ መስከረም 02, 2018 71

ቻይና በሚቀጥለው ሳምንት የቤጂንግ ዢያንግሻን ፎረም ላይ ከ100 በላይ ሀገራት የመከላከያ ባለስልጣናትን እንደምታስተናግድ አስታወቀች።

ይህ የሀገሪቱ ትልቁ የፀጥታ ኮንፈረንስ መሆኑ ተገልጿል።

የቻይና መከላከያ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ ከፍተኛ ኮሎኔል ጂያንግ ቢን እንደተናገሩት "ቬትናም፣ ሲንጋፖር፣ ሩሲያ፣ ፈረንሳይ፣ ናይጄሪያ እና ብራዚልን ጨምሮ ከ100 በላይ ሀገራት ከዓለም አቀፍ እና አህጉራዊ ድርጅቶች ተወካዮች ጋር ለመገኘት ማረጋገጫ ሰጥተዋል" ብለዋል።


#EBC #ebcdotstream #China