Search

የ7ኛው ጠቅላላ ምርጫ የፓርቲዎች ክርክር፤ የሐሳብ የበላይነትና የዴሞክራሲያዊ ሥርዓት ግንባታ ማሳያ

ዓርብ የካቲት 27, 2018 67

በኢትዮጵያ እየተካሄደ ያለው የ7ኛው ጠቅላላ ምርጫ የፓርቲዎች የፖሊሲ ክርክር፣ መራጩ ሕዝብ በስሜት ሳይሆን በምክንያትና በዕውቀት ላይ ተመስርቶ ድምፁን እንዲሰጥ ትልቅ ዕድል እየፈጠረ ይገኛል።
ፓርቲዎች በኢኮኖሚ፣ በሰላምና ጸጥታ እንዲሁም በማኅበራዊ ጉዳዮች ላይ ያላቸውን አማራጭ መፍትሔዎች ለሕዝብ ይፋ ማድረጋቸው፣ ለኢትዮጵያ ዴሞክራሲያዊ ሂደት አዲስ ተስፋን ሰንቋል።
እንደ ፖለቲካ ተንታኞች ገለጻ፣ እነዚህ ክርክሮች ለሀገር ግንባታ የሚከተሉትን 5 ቁልፍ ፋይዳዎች ያስገኛሉ፦
በመረጃ ላይ የተመሠረተ ውሳኔ፦ ዜጎች የፓርቲዎችን ፕሮግራም መዝነውና ለሀገሪቱ ችግሮች የሚያቀርቡትን አማራጭ መፍትሔዎች አይተው በነፃነት እንዲወስኑ ይረዳቸዋል።
የፖለቲካ ባሕልን ማዘመን፦ የ"ጠመንጃ" ፖለቲካን በ"ሐሳብ" ፖለቲካ በመተካት፣ ልዩነቶችን በሥነ-ምግባርና በጠረጴዛ ዙሪያ የመፍታት የሰለጠነ ባህልን ያነግሳል።
ተጠያቂነትን ማጠናከር፦ ፓርቲዎች በክርክሩ ወቅት የሚገቧቸውን ቃል በሰነድ ተመዝግበው የሚቀሩ በመሆናቸው፣ ወደ ሥልጣን ሲመጡ ሕዝቡ በገባችሁት ቃል መሠረት አልሠራችሁም ብሎ እንዲጠይቃቸው መነሻ ይሆናል።
ሰላማዊ የሥልጣን ሽግግር፦ የሐሳብ ነፃነት ሲከበርና ሁሉም ወገን ሲሰማ ቅሬታዎች ወደ ግጭት የማምራት ዕድላቸው ይቀንሳል፤ ይህም ለምርጫው ሰላማዊነትና ውጤቱ በሁሉም ዘንድ ተቀባይነት እንዲኖረው ያግዛል።
የዜጎችን የፖለቲካ ንቃት ማሳደግ፦ በተለይ ወጣቱ ስለ ሀገር ግንባታና ስለ መብቶቹ ያለው ግንዛቤ እንዲሰፋ በማድረግ፣ ዜጎች በሀገራዊ ጉዳዮች ላይ ንቁ ባለቤት እንዲሆኑ ያነሳሳል።
ይህ የሐሳብ ክርክር የዴሞክራሲያዊ ሥርዓት ግንባታችንን ከማፋጠኑም በላይ፣ ከምርጫ በኋላ ለሚመጣው መንግሥት የተጠያቂነት መሠረት የሚጥል በመሆኑ ለሀገራዊ መረጋጋትና እድገት ትልቅ ድርሻ አለው።