Search

የባሕር በር ባለቤትነት፡ የኢትዮጵያ የኢኮኖሚና የሉዓላዊነት ማኅተም

ዓርብ የካቲት 27, 2018 88

ኢትዮጵያ የባሕር በር ባለቤት መሆኗ ለሀገሪቱ ዘላቂ ህልውና እና ለወደፊት ዕድገቷ ስትራቴጂካዊ ፋይዳው እጅግ ከፍተኛ ነው።
በሕዝብ ብዛቷ በዓለም ወደብ ከሌላቸው ሀገራት ቀዳሚ የሆነችው ኢትዮጵያ፣ ይህንን ታሪካዊ ክፍተት በመሙላት የኢኮኖሚ ነጻነቷን ማረጋገጥ እንደሚገባት ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በተደጋጋሚ አፅንኦት ሰጥተዋል።
ለኢትዮጵያ የባሕር በር የማግኘት ጉዳይ በሦስት ዋና ዋና ምክንያቶች የህልውና ጥያቄ ነው፦
1. የኢኮኖሚ ሉዓላዊነት እና የሰማያዊ ኢኮኖሚ ዕድል- በአሁኑ ወቅት ለወደብ አገልግሎት በየቀኑ የሚወጣውን በሚሊዮን የሚቆጠር ዶላር በማስቀረት ለታላላቅ የልማት ፕሮጀክቶች ማዋል ያስችላል።
ይህም የውጭ ኢንቨስትመንትን በመሳብ ምርቶችን በቀላሉ ለዓለም ገበያ ለማቅረብ መተማመንን ይፈጥራል። በተጨማሪም የዓሳ ሀብትንና የባሕር ማዕድናትን በማልማት "ሰማያዊ ኢኮኖሚን" እውን ለማድረግ መሠረት ይሆናል።
2. ጂኦ-ፖለቲካዊ ተጽዕኖ እና የዲፕሎማሲ አቅም -የባሕር በር ባለቤት መሆን በዓለም አቀፍ መድረክ የመደራደር አቅምን ከመጨመሩም በላይ፣ ስትራቴጂካዊ በሆኑ የባሕር መስመሮች ላይ አገራዊ ተጽዕኖን ያሳርፋል። ይህም ኢትዮጵያ በቀጣናዊ ፖለቲካ ውስጥ ያላትን ቁልፍ ሚና ወደ ላቀ ደረጃ ያሸጋግረዋል።
3. ብሔራዊ ደህንነት እና የባሕር ኃይል ግንባታ- ጠንካራ የባሕር ኃይል በመገንባት ሀገሪቱን ከባሕር አቅጣጫ ከሚሰነዘሩ ጥቃቶች፣ ከሕገ-ወጥ ዝውውር እና ከባሕር ላይ ዘረፋ ለመጠበቅ አስተማማኝ ዋስትና ይሰጣል። ይህም የዜጎችን ደህንነት ከየብስ ባለፈ በውኃ ላይ ለማረጋገጥ ወሳኝ ነው።
በሃይማኖት ከበደ