ስርጭት ከጀመረ ዛሬ መስከረም 2 ቀን 2018 ዓ.ም 90 ዓመት የሞላው የኢትዮጵያ ሬዲዮ የምስረታ በዓሉን እያከበረ ይገኛል፡፡
ሀገር በትውልድ ቅብብሎሽ ባትገነባ ኖሮ የኢትዮጵያ ሬዲዮም 90ኛ ዓመቱ ላይ አይደርስም ነበር ሲሉ የኢቢሲ ዋና ሥራ አስፈፃሚ አቶ ቢኒያም ኤሮ ጂማ ገልጸዋል።
ሬዲዮ ሀገር የምትሄድበትን መንገድ፣ ብሔራዊ ጥቅሟን እና ሀገረ መንግስት እየተገነባ ያለበትን ሁኔታ ለሕዝቡ የሚያደርስ ወሳኝ መሳሪያ መሆኑን አንስተዋል።
ትርክት ሀገርን ሊሰራም ሊያፈርስም ይችላል ያሉት ዋና ሥራ አስፈፃሚው፤ ሬዲዮን ቁልፍ መሳሪያ በማድረግ ኅብረ ብሔራዊነትን መሰረት ያደረገ ገዢ ትርክት በህዝቦች ዘንድ ማስረፅ ይገባል ብለዋል።
ኢትዮጵያ ትልቅ ሀገር እንደመሆኗ የኢትዮጵያ ሬዲዮ ተደራሽነቱን ይበልጥ በማስፋት ለሁሉም ሕብረተሰብ ለመድረስ እንደሚሰራም ገልፀዋል።
የኢትዮጵያ ሬዲዮ የሁሉም ኢትዮጵያዊ የበኩር የመረጃ ምንጭ መሆኑን በመግለፅም፤ በተለያዩ ሚኒ ሚዲያዎች ከመሳተፍ ጀምሮ በሙያው ብዙ ነገር እንድሰራ መነሳሳትን ፈጥሮልኛል ብለዋል።
የኢቢሲ የሬድዮ ዘርፍ ምክትል ዋና ሥራ አስፈፃሚ ጋዜጠኛ ሰናይት ሐይሌ በበኩላቸው፤ የኢትዮጵያ ሬድዮ ከኢትዮጵያ ውጣ ውረዶች ጋር አብሮ 90 ዓመታትን አሳልፏል ብለዋል፡፡
በዓለም ላይ ጥቂት ሀገራት ብቻ የሬድዮ ጣቢያ በነበራቸው ወቅት የተመሰረተው የሬዲዮ ጣቢያው፤ በወቅቱ በቅኝ ግዛት ውስጥ ለነበሩ አፍሪካውያን ድምፅ መሆን የቻለ ነበር ብለዋል፡፡
በብዙ መንገድ ፈር ቀዳጅ የሆነው የሬድዮ ጣቢያው፣ በኪነ-ጥበብ ዘርፉም በርካታ ባለሞያዎችን ማፍራት መቻሉን አንስተዋል፡፡
የበርካታ ድምፃውያን ሥራም ጣቢያው በነበረው የሙዚቃ የኦርኬስትራ ባንድ እንዲቀረጽ በማድረግ ለሕዝብ ተደራሽ ሲያደርግ መቆየቱን ጠቅሰዋል፡፡
በሴራን ታደሰ
#ethiopianradio #radio #90th #ebcdotstream #anniversary