Search

ቡርኪና ፋሶ ለመላው አፍሪካ ተጓዦች የቪዛ ክፍያ አነሳች

ዓርብ መስከረም 02, 2018 66

 

ቡርኪና ፋሶ ለመላው አፍሪካ ተጓዦች የቪዛ ክፍያን ማንሳቷን አስታውቃለች።

 

ይህም እርምጃ በአፍሪካ አህጉር የሚደረገውን የሰዎችና የሸቀጦች እንቅስቃሴ ለማቀላጠፍ ያለመ ነው ተብሏል።

 

የሀገሪቱ የፀጥታ ሚኒስትር ማሃማዱ ሳና እንደተናገሩት፣ ከእንግዲህ በኋላ ከማንኛውም የአፍሪካ ሀገር ወደ ቡርኪና ፋሶ ለመጓዝ የሚፈልግ ማንኛውም ዜጋ ለቪዛ ክፍያ ምንም አይነት ገንዘብ አይከፍልም። 

 

ሆኖም፣ ቪዛው በነፃ የሚሰጥ ቢሆንም፣ አፍሪካውያን ጎብኚዎች የቪዛ ማመልከቻ ማቅረብ እና ማረጋገጫ ማግኘት እንዳለባቸው ሚኒስትሩ አብራርተዋል።

 

ይህ ውሳኔ ቡርኪና ፋሶን ከጋና፣ ሩዋንዳ እና ኬንያ ጋር የአፍሪካን ውህደት ለማስፋፋት የጉዞ ገደቦችን ከተቀላቀሉ ሀገራት ተርታ እንድትሰለፍ አድርጓታል።

 

በሰለሞን ገዳ