Search

ዕድሜው ለትምህርት የደረሰ ልጅን ወደ ትምህርት ቤት አለመላክ ያስጠይቃል

ዓርብ መስከረም 02, 2018 50

ወላጀች ወይም አሳዳጊዎች ዕድሜው ለትምህርት የደረሰ ልጅን ወደ ትምህርት ቤት አለመላክ በሕግ እንደሚያስጠይቅ ተገንዝበው የሚጠበቅባቸውን ኃላፊነት እንዲወጡ ትምህርት ሚኒስቴር አሳስቧል፡፡
ከመስከረም 5 ቀን 2018 ዓ.ም ጀምሮ ሁሉም ትምህርት ቤቶች ለትምህርት ክፍት ሆነው የመማር ማስተማር ሥራቸውን እንደሚጀሩም ሚኒስቴሩ አስታውቋል።
በኢትዮጵያ ዕድሜያቸው ለትምህርት የደረሱ ከ7 ሚሊዮን በላይ ሕጻናት በተለያዩ ምክንያቶች ከትምህርት ገበታ ውጪ መሆናቸውን ሚኒስቴሩ መግለጹ ይታወቃል።
የአንደኛ ደረጃ ትምህርት ነጻና ግዴታ መሆኑን በመገንዘብም እነዚህን ልጆች ወደ ትምህርት ቤት መላክ ሀገራዊ ንቅናቄን በመቀላቀል የዜግነት ግዴታን መወጣት አስፈላጊ መሆኑም አመላክቷል።
ወላጆች፣ አሳዳጊዎች፣ ሕብረተሰቡና ባለድርሻ አካላት ዕድሜያቸው ለትምህርት የደረሱ ልጆች ከትምህርት ገበታ ውጭ እንዳይሆኑ ሊረባረቡ እንደሚገባ በሚኒስቴሩ የትምህርት ፕሮግራሞችና ሥርዓት ማሻሻል ዴስክ ኃላፊ ዳዊት አዘነ ጠይቀዋል።
ከነሐሴ 1 ቀን 2017 ዓ.ም ጀምሮ በመላው ሀገሪቱ የትምህርት ምዝገባ እና ተጓዳኝ ተግባራት በጥሩ ሁኔታ እየተከናወኑ መሆኑም ተጠቁሟል።