ታላቁ የሕዳሴ ግድብ ኢትዮጵያን ብቻ ሳይሆን ቀጣናዊ የኢኮኖሚ ትስስርን በማጠናከር ሌሎች የአፍሪካ ሀገራትን ጭምር ተጠቃሚ የሚያደርግ ነው በኢትዮጵያ የጀርመን ምክትል አምባሳደር ፈርዲናንድ ፎን ቫሄ (ዶ/ር) ገለጹ።
ከግድቡ ምረቃ ጋር በተያያዘ ከኢዜአ ጋር ቆይታ ያደረጉት ምክትል አምባሳደሩ፥ ግድቡ ከፍተኛ የኤሌትሪክ ኃይል የማመንጨት አቅም ያለው መሆኑን ገልጸው፤ ጎረቤቶቿን ጨምሮ የአፍሪካ ሀገራት ከኢትዮጵያ ጋር በትብብር ከሠሩ ተጠቃሚ መሆን እንደሚችሉ ተናግረዋል።
ታላቁ የሕዳሴ ግድብ በኢትዮጵያውያን ትብብር እውን መሆኑን አውቃለሁ ያሉት ምክትል አምባሳደሩ፤ የግድቡ ግንባታ ተጠናቅቆ ለምረቃ መብቃቱ የሚያኮራ ነው ብለዋል።
በኢትዮጵያ የተከናወኑ የኢኮኖሚ ማሻሻያዎች ሀገሪቱን ለውጭ ቀጥታ ኢንቨስትመንት የተመቸች እንዳደረጓትም ተናግረዋል።
በኢትዮጵያ የካርበን ልቀትን ለመቀነስ እና የታዳሽ ኃይል አጠቃቀምን ለማስፋት የሚከናወኑ ሥራዎችን መመልከታቸውን ገልጸው፤ ይህም የሚበረታታ ተግባር ነው ብለዋል።
ኢትዮጵያና ጀርመን በፀሐይና በሌሎች ታዳሽ የኃይል አማራጮች ላይ በጋራ ጥናትና ምርምር እየሠሩ እንደሚገኙም ምክትል አምባሳደሩ አንስተዋል።
#Ethiopia #GERD #Inauguration