Search

ያለአንዳች ልዩነት፣ ያለማንም ድጋፍ የሠራነው ግድብ በአጭር ጊዜ ከድህነት እንደምንወጣ አብሳሪ ነው

ዓርብ መስከረም 02, 2018 38

ታላቁ የሕዳሴ ግድብ ኢትዮጵያውያን በአጭር ጊዜ ከድህነት ለመላቀቅ ያላቸውን የተጨበጠ ተስፋ የሚያመላክት ሐውልት ነው ሲሉ የባህርዳር ከተማ ነዎሪዎች ገለጹ።

እናቶች ጭምር ከመቀነታቸው ፈትተው የገነቡት ግድቡ ግንባታው ተጠናቅቆ መልሶ የእናቶችን የማገዶ ጭስ ዕንባ ለማበስ መመረቁ ለብዙዎች ተስፋን የፈነጠቀ ነው ብለዋል ነዋሪዎቹ ለኢቲቪ ሲናገሩ።

ሲደረጉብን የነበሩ ፈርጀ ብዙ ጫናዎችን በኅብረት ቆመን፣ በፅናት ተቋቁመን በማለፍ ለምረቃው መድረሳችን የዓድዋ ድልን የሚያስታውሰን ዳግማዊ ዓድዋ ነው ብለዋል።

መላ ኢትዮጵያውያን ያለአንዳች ልዩነት ተረባርበን በራስ አቅም ያለማንም ድጋፍ እውን ያደረግነው ግድቡ ከድህነት ወጥተን አንገታችንን ቀና አድርገን የምንኖርበት ዘመን መቃረቡን አብሳሪ ነው ሲሉ ገልጸውታል።

ላለፉት 14 ዓመታት ያለማቋረጥ ለግድቡ ድጋፍ ሲያደርጉ መቆየታቸውን ጠቅሰው፤ ህዝባዊ ተሳትፎው በሌሎች መሰል ፕሮጀክቶች ላይም ተጠናክሮ መቀጠል ያለበት ነው ብለዋል።

በሜሮን ንብረት

#Ethiopia #GERD #Inauguration