የ2017 የ12ኛ ክፍል ማጠናቀቂያ ፈተና ውጤት በነገው ዕለት ይፋ ይሆናል።
የትምህርት ሚኒስቴር እንዳስታወቀው፤ የፈተና ውጤቱን አስመልክቶ በነገው ዕለት ከ10 ሰዓት ጀምሮ ለመገናኛ ብዙሃን ማብራሪያ ይሰጣል።
በተፈጥሮ ሳይንስ እና በማህበራዊ ሳይንስ በአጠቃላይ 608 ሺህ 742 ተማሪዎች ፈተናውን ወስደዋል።
የ2017 የትምህርት ዘመን የ12ኛ ክፍል ማጠናቀቂያ ፈተና ከሰኔ 23 እስከ ሐምሌ 8 ቀን 2017 ዓ.ም በሀገር አቀፍ ደረጃ መሰጠቱ ይታወሳል።