Search

ኢትዮጵያ የጀመረችው የማንሰራራት ጎዞ በልጆቿ ብርቱ ጥረት ወደ ብልፅግና ይደርሳል

እሑድ መስከረም 04, 2018 58

የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል እና የአሶሳ ከተማ አስተዳደር ከፍተኛ አመራሮች እንዲሁም የከተማው ነዋሪዎች የተሳተፉበት የታላቁ የኢትዮጵያዳሴ ግድብ ምረቃን የሚደግፍ የጎዳና ላይ ጉዞ እና የአካል ብቃት እንቅስቃሴ ተካሂዷል።

በአሶሳ ከተማ ዛሬ ማለዳ በተካሄደው ልዩ የአካል ብቃት እንቅስቃሴ ተሳታፊዎች "ግድቡን እንደጀመርነው በይቻላል መንፈስ ጨርሰነዋል፣ ዘመኑ ኢትዮጵያ የምታንሰራራትበት ነው፣ አንድነታችንን በማጠናከር ሌሎች ታላላቅ ፕሮጀክቶችን ጀምረን እንጨርሳለን" የሚሉ እና ሌሎችም መፈክሮች አሰምተዋል።

በዚሁ የአካል ብቃት እንቅስቃሴ ላይ የተሳተፉት አመራሮችና የተለያዩ የማህበረሰብ ተወካዮች ግድቡ በኢትዮጵያውያን የተባበረ ክንድ እውን በመሆኑ የተሰማቸውን ደስታ ገልጸዋል።

ኢትዮጵያ የጀመረችው የማንሰራራት ጎዞ በልጆቿ ብርቱ ጥረት ወደ ብልፅግና ይደርሳል ያሉት ተሳታፊዎቹ፤ እስካሁን የተገኙ ሀገራዊ ስኬቶችን አጠናክሮ ለማስቀጠል ሁሉም ተግቶ ሊሰራ ይገባል ሲሉ መልዕክት አስተላልፈዋል።

በጀማል አሕመድ

#EBCdotstream #Ethiopia #GERD #PublicRally