በጋምቤላ ክልል ታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ ግንባታ በስኬት መጠናቀቁን በማስመልከት የጎዳና ላይ ሩጫ ተካሂዷል።
በዕለቱ የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር ወይዘሮ አለሚቱ ኡሞድ በተገኙበት በጋምቤላ ከተማ የአካል ብቃት እንቅስቃሴም ተከናውኗል።
በመርሐ-ግብሩ ላይ ከከፍተኛ የመንግሥት ሀላፊዎች በተጨማሪ አትሌት ኢብራሂም ጄይላንን ጨምሮ የተለያዩ እንግዶችም ተሳትፈዋል።
ታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ በሕዝቧ ርብርብ በስኬት መጠናቀቁ በጋምቤላ ክልል እና ከተማ ነዋሪዎች ዘንድ ትልቅ ደስታን ፈጥሯል።
ይህን ተከትሎም በክልሉ በተለያዩ አካባቢዎች ህብረተሰቡን ያሳተፉ የተለያዩ መርሐ-ግብሮች በመከናወን ላይ ናቸው።
በሚፍታህ አብዱልቃድር
#EBCdotstream #Ethiopia #GERD #PublicRally