የደቡብ ዕዝ የተሰጠውን አገራዊና ተቋማዊ ግዳጅ በብቃት እየፈፀመ እንደሚገኝ የዕዙ ዋና አዛዥ ሌተናል ጄነራል ሰለሞን ኢተፋ ተናገሩ።
ጄነራል መኮንኑ ይህን የተናገሩት የደቡብ ዕዝ ማሰልጠኛ ማዕከል ያሰለጠናቸውን 2ኛ ዙር የአመራር፣ ልዩ ልዩ ሙያና መሳሪያ ምድብተኛ ሰልጣኞችን ባስመረቀበት ወቅት ነው።
መከላከያ ሠራዊት ከዚህ ቀደም ያጋጠሙ የፀጥታ ችግሮችን በህብረትና በአንድነት መቀልበስ ችሏል ያሉት ሌተናል ጄነራል ስለሞን ኢተፋ፤ የደቡብ ዕዝም በግዳጅ ቀጣናው አሸባሪውን የሸኔ ቡድን እና ፅንፈኛ ኃይሎችን በመደምሰስ ተልዕኮውን ፈፅሟል ብለዋል።
በተቋማዊ ሪፎርሙ ዘመኑን የዋጀ ፕሮፌሽናል ሠራዊት ለማፍራት በርካታ ሥራዎች እየተከናወኑ መሆኑንም ገልጸዋል።
የደቡብ ዕዝ ማሰልጠኛ ማዕከል ዋና አዛዥ ኮሎኔል ቦጋለ ተገኔ በበኩላቸው፥ በዛሬው ዕለት የተመረቁት ሰልጣኞች በሰለጠኑበት ዘርፍ በቂ እውቀት እንዲያገኙ ተደርጓል ብለዋል።
በወንድወሰን አፈወርቅ
#EBCdotstream #Ethiopia # DefenseForce #SouthernCommand