Search

በቀጣይ 5 ዓመታት የአዲስ አበባ ሙስሊም ማህበረሰብን አንድነት የሚያጠናክሩ ተግባራት ይከናወናሉ - ሼይህ ሱልጣን አማን ኤባ

እሑድ መስከረም 04, 2018 42

የአዲስ አበባ እስልምና ጉዳዮች ከፍተኛ ምክር ቤት የምስጋና እና የእውቅና ፕሮግራም በዛሬ ዕለት ተካሂዷል።

በቅርቡ የተካሄደው የከፍተኛ ምክር ቤቱ ምርጫ በስኬት እንዲከናወን አስተዋፅዖ ላበረከቱ አካላት ምስጋና እና እውቅና በተሰጠበት መድረክ፤ የከፍተኛ ምክር ቤቱ ፕሬዚዳንት ሆነው በድጋሚ የተመረጡት ሼይህ ሱልጣን አማን ኤባ ምርጫው ታላቅ ሀላፊነትን የጣለብን ነው ብለዋል።

በቀጣይ 5 ዓመታት የአዲስ አበባ ሙስሊም ማህበረሰብን አንድነት የሚያጠናክሩ ተግባራት እንደሚከናወኑ ተመራጩ ፕሬዚዳንት አክለው ገልጸዋል።

የአዲስ አበባ እስልምና ጉዳዮች ከፍተኛ ምክር ቤት ምርጫ ቦርድ ሰብሳቢ ጅብሪል ኡስማን በበኩላቸው፥ ምርጫው ፍትሃዊ እንደነበር ገልጸው፤ የምርጫ ሂደቱም የጋራ ችግሮችን በአንድነት ለመፍታት መንገድ አመላክቶናል ብለዋል።

በሙሀመድ አልቃድር

#EBCdotstream #AddisAbaba #IslamicAffairs #Election