Search

የ12ኛ ክፍል ውጤት መግለጫ እየተሰጠ ነው

እሑድ መስከረም 04, 2018 237

120 የ12ኛ ክፍል ተማሪዎች ለመኮረጅ ሲሞክሩ ተይዘው ውጤታቸው መሰረዙን የትምህርት ሚኒስትሩ ፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋ ገለጹ።

የትምህርት ሚኒስትሩ የ12ኛ ክፍል ውጤትን በተመለከተ መግለጫ እየሰጡ ነው።

በዚህም የፈተና ሂደቱ በአቋራጭ የመክበር አስተሳሰብ ምን ያክል ስር እንደሰደደ ማሳያ እንደሆነ ጠቁመው፣ በዚህ ዓመት ይህ አስተሳሰብ የቀነሰ መሆኑን ተናግረዋል። 

የ2017 ዓ.ም ትምህርት ዘመን የ12ኛ ክፍል ማጠናቀቂያ ከፍተኛ ውጤት የምናካሂደው ሪፎርም ውጤት የሚታይበት መሆኑን ገልጸዋል።

መድረስ የምንሻበት ቦታ መድረስ ካስፈለገ በትምህርት ዘርፉ ላይ ለውጥ መምጣት አለበት ያሉት ፕሮፌሰር ብርሃኑ፤ የፈተና አሰጣጡ ጥሩ እንደነበር ተናግረዋል።

በለሚ ታደሰ