Search

በ2017 ዓ.ም የ12ኛ ክፍል ማጠናቀቂያ ፈተና 8.4 በመቶ ተማሪዎች 50 በመቶ እና ከዚያ በላይ አምጥተዋል - ፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋ

እሑድ መስከረም 04, 2018 100

በ2017 ዓ.ም ትምህርት ዘመን የ12ኛ ክፍል ማጠናቀቂያ ፈተና 8.4 በመቶ ተማሪዎች 50 በመቶ እና ከዚያ በላይ ውጤት ማስመዝገባቸውን የትምህርት ሚኒስትሩ ፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋ ገለጹ፡፡
ሚኒስትሩ የትምህርት ዘመኑን የ12ኛ ክፍል ማጠናቀቂያ ፈተና ውጤትን አስመልክተው መግለጫ እየሰጡ ይገኛሉ፡፡
50 በመቶ እና ከዚያ በላይ ውጤት ካስመዘገቡት መካከል የማኅበራዊ ሳይንስ ተፈታኞች 5.2 በመቶ፣ ተፈጥሮ ሳይንስ ተፈታኞች ደግሞ 11.4 በመቶ የ እንደሆኑ ፕሮፌሰር ብርሃኑ ጠቅሰዋል፡፡
585 ሺህ 882 ተማሪዎች ፈተናውን ተፈትነዋል፡፡
በለሚ ታደሰ