የ2017 ዓ.ም ትምህርት ዘመን የ12ኛ ክፍል ማጠናቀቂያ ፈተና ውጤት ካለፉት ዓመታት ጋር ሲነጻጸር ለውጥ መምጣቱን የሚያሳይ ነው ሲሉ የትምህርት ሚኒስትሩ ፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋ ገልጸዋል።
ክልሎች ለውጤቱ መሻሻል በርትተው እየሠሩ እና ለውጥ እያመጡ እንደሚገኙም አመላካች ነው ሲሉ ተናግረዋል።
ተማሪዎቹም በርትተው የመሥራት ባህል እያሳደጉ መምጣታቸውን ማሳያ እንደሆነ ነው በመግለጫቸው የጠቀሱት።
በለሚ ታደሰ