የፕላንና ልማት ሚኒስትሯ ፍፁም አሰፋ (ዶ/ር) በአማራ ክልል የመሶብ የአንድ ማዕከል አገልግሎት የምረቃ መርሃ ግብር ላይ ተገኝተዋል።
በወቅቱም ማዕከሉ ዜጎች ከመንግሥት የሚፈልጓቸውን አገልግሎቶች በጥራትእና በቴክኖሎጂ በታገዘ መልኩ የሚሰጥበት ነው ብለዋል።
ይህም የአገልግሎቶችን ተደራሽነት እና ቅልጥፍና ከማሳደግ አንፃር አንድ ደረጃ ከፍ የሚያደርግ ስለመሆኑም ገልፀዋል።
ከዚህ በፊት በተለያዩ አካባቢዎች የአገልግሎት አሰጣጥ ቅልጥፍና ላይ ቅሬታዎች ሲነሱ እንደነበር አስታውሰው፤ ችግሩን ለመፍታት መሶብ አይነተኛ መንገድ መሆኑን አንስተወዋል።
በዚህም መንግሥት የሕዝብን ጥያቄ በአግባቡ ለመመለስ ያለውን ቁርጠኝነት በመሶብ የአንድ ማዕከል አገልግሎት አስመስክሯል ብለዋል።
በሳሙኤል ወርቃየሁ