በከፍታው በዓለም ቁጥር አንድ የሆነው የቻይናው ድልድይ ግንባታው ተጠናቅቆ ለአገልግሎት ክፍት ሆኗል።
በዚህም ቻይና ወንዝ ይለያቸው የነበሩ ሁለት ተራራማ ስፍራዎችን በዘመናዊ ድልድይ አማካኝነት ፈጣን የትራንስፖርት አገልግሎት እንዲያገኙ አድርጋለች።
በቻይና ሁዋጂያንግ ሸለቋማ ስፍራ ላይ የተገነባው ድልድዩ 2 ሺ 890 ሜትር ርዝመት ያለው ሲሆን፤ ድልድዩ ከስሩ ከሚገኘው ቤይፓን ወንዝ ወደላይ የ625 ሜትር ከፍታ እንደሚርቅ ሲጂቲኤን ዘግቧል።
ተንጠልጣይ ድልድዩ ከዚህ ቀደም 2 ሰዓታት የሚፈጀውን ጉዞ ወደ 2 ደቂቃዎች ይቀንሳልም ነው የተባለው።
ቀደም ሲል የትራንስፖርት አገልግሎት የማያገኙ ግዛቶችን በፍጥነት መንገድ የሚያገናኘው ፕሮጀክቱ ለአካባቢው ኢኮኖሚያዊ እድገት፣ ለቱሪዝም እና ማኅበራዊ ልማት በጎ ጎን እንደአለው በዘገባው ተመላክቷል።
ከዚህ ቀደም ከመሬት በነበረው ከፍታ በዓለም ትልቁ የነበረው ድልድይ በቻይና ይገኝ የነበረ ሲሆን፤ ከመሬት በ565 ሜትር ርቀት አለው።
በሴራን ታደሰ